ላለፉት አምስት ዓመታት የደሴ ከተማ ከንቲባ በመሆን ከተማዋን በልማት፣ በሰላም እና በማህበራዊ አገልግሎቶች ግንባር ቀደም የማህበረሰብ ተ ተቀባይነት ባለው አመራር ሲመሩ የቆዩት አቶ ሳሙዔል ሞላልኝ፣ ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባነት በመሾማቸው ምክንያት በደሴ ከተማ ጠቅላላ አመራርና ማህበረሰብ ዘንድ ደማቅ የሽኝት መርሃ ግብር ተካሂዶላቸዋል።
በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ሀገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የሽኝት መርሀ ግብሩ ተካሂዷል።
የደሴ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አሸናፊ ዓለማየሁ የ5 ዓመታት የአመራር ዘመን አሻራዎች አቶ ሳሙዔል ሞላልኝ ደሴን በከንቲባነት በመሩበት አምስት ዓመታት በጽናትና በጥበብ በመምራት በርካታ ውጤቶች ማስመዝገብ ችለዋል ሲሉ አመስግነዋቸዋል።
በሽኝት መርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ የደሴ ከተማ አመራሮች አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ስጦታዎችን አበርክተዋል።









