በደሴ ከተማ ልማትና ሰላም ላይ አሻራቸውን ያኖሩት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በታላቅ ሽኝት ተሸኙ

​ላለፉት አምስት ዓመታት የደሴ ከተማ ከንቲባ በመሆን ከተማዋን በልማት፣ በሰላም እና በማህበራዊ አገልግሎቶች ግንባር ቀደም የማህበረሰብ ተ ተቀባይነት ባለው አመራር ሲመሩ የቆዩት አቶ ሳሙዔል ሞላልኝ፣ ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባነት በመሾማቸው ምክንያት በደሴ ከተማ ጠቅላላ አመራርና ማህበረሰብ ዘንድ ደማቅ የሽኝት መርሃ ግብር ተካሂዶላቸዋል።

​በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ሀገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የሽኝት መርሀ ግብሩ ተካሂዷል።

የደሴ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አሸናፊ ዓለማየሁ ​የ5 ዓመታት የአመራር ዘመን አሻራዎች ​አቶ ሳሙዔል ሞላልኝ ደሴን በከንቲባነት በመሩበት አምስት ዓመታት በጽናትና በጥበብ በመምራት በርካታ ውጤቶች ማስመዝገብ ችለዋል ሲሉ አመስግነዋቸዋል።

​በሽኝት መርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ የደሴ ከተማ አመራሮች አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ስጦታዎችን አበርክተዋል።

34 views 0 likes
Share Telegram WhatsApp