Back to News

Uncategorized September 30, 2026

አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ኾነው ተሾሙ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግሥት ምሥረታ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የፕላን ልማት ቢሮ አድርጎ ሾሟል።

አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ባለፉት ዓመታት የደሴ ከተማ አሥተዳደርን በተቀዳሚ ምክትል ከንቲባነት መርተዋል። በመሪነት ዘመናቸውም በደሴ ከተማ ውጤታማ ሥራዎችን ሠርተዋል።

በከተማዋ የረጅም ዓመታት የሕዝብ ጥያቄዎች እንዲፈቱ፣ ከተማዋ ታሪኳን ጠብቃ እንድትዘምን እና የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻል ስኬታማ ሥራዎችን ሠርተዋል።

ዛሬ ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ኾነው ተሹመዋል

39 views 0 likes
Share Telegram WhatsApp

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *